የኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር እና ዳውን ሲንድሮም በህጻናትና ልጆች ዕድገት ላይ የተለያዩ ተጽእኖዎች ያላቸው የእድገት ሁኔታዎች ናቸው። ይህ ማለት እነዚህ የእድገት ሁኔታዎች በአእምሮ ዕድገት እንዲሁም በማህበራዊ መስተጋብር እና ግንኙነት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ የነርቭ እድገት ሁኔታዎችን ሊያካትት ይችላል።


ይህ ጽሑፍ ኦቲዝምንና ዳውን ሲንድሮምን እንደ ሁለት በተለያዩ መንገዶች የሚነሱ የእድገት ችግሮች እንደሆኑ ያሳያል፡፡

  • ኦቲዝም፡ በልጆች ንግግር፣ አስተያየትና ባህሪያት ላይ ተፅእኖ የሚያሳድር፤ ውስብስብ የዕድገት ችግር ሲሆን:–
  • ዳውን ሲንድሮም፡ ደግሞ በክሮሞዞም 21 ላይ ቀድሞ ከነበሩት መደበኛና ጥንድ ክሮሞዞሞች ላይ ሌላ (ሶስተኛ) ተጨማሪ አንድ ቅጂ ክሮሞዞም መፈጠር ምክንያት የሚነሳ የዘረመል አፈጣጠር ችግር ነው። ይህም በአካልና በአእምሮ እድገት ላይ ተፅእኖ ይኖረዋል።

የበለጠ ዘርዘር አድርጎ ለመግለፅ ፡-

የኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር (ASD)፡-

ምክንያት፡

የአንጎል ዕድገት በሚካሄድበት ወቅት በሚፈጠሩ የታወቁና አንዳንዶቹ ደግሞ ገና ያልታወቁ ችግሮች ምክንያት፣ በተለይም ከልጆች ማህበራዊ ግንኙነት እና ተግባቦት ጋር በተያያዘ የሚፈጠር የዕድገት ውስንነት ሲሆኑ፣ ከታወቁት ምክንያቶች የዘረመል ዕድገት ውስንነት አንዱ ነው። ትክክለኛው መንስኤ ግን አሁንም በምርምር ላይ ያለ ጉዳይ ነው። 

ምልክቶች፡-

በማህበራዊ መስተጋብር፣ ግንኙነት እና ተግባቦት ላይ ተደጋጋሚ ባህሪያት ወይም ፍላጎቶች ላይ የሚታዩ ችግሮች።  ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች (ግለሰቦች) ማህበራዊ ምልክቶችን ለመረዳት፣ ክትትል ማድረግ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ ተጠቂዎች (ታማሚዎች) ከሰዎች ጋር ያላቸው መስተጋብር ለየት ያለ ወይም ግለኛ መሆን፣ ንግግሮችን መጀመር እና ማቆየት እና አንድን ነገር በጣም በተደጋጋሚ መተግበር ወይም ለነገሮች ትኩረት አለመስጠት ሊሆኑ ይችላሉ። 

ተጽዕኖ፡

ማህበራዊ፣ ስሜታዊ እና የመግባቢያ ችሎታዎችን ጨምሮ የተለያዩ ክህሎቶችን ሊጎዳ ይችላል፣ እና የስሜት ህዋሳትንም ሊያካትት ይችላል። 

አካላዊ ባህሪያት፡-

ከኦቲዝም ጋር የተቆራኘ ምንም የተለየ አካላዊ ገፅታዎች የሉም። 

ዳውን ሲንድሮም:–

ምክንያት፡ 

ጄኔቲክ፣ በተለይም ተጨማሪ የክሮሞዞም 21 (ትሪሶሚ 21) ወይም በአማርኛው በ 21ኛው ህብለበራሒ ላይ ሶስተኛ ተጨማሪ ቅጂ መኖር (መፈጠር) ነው። 

ምልክቶች፡ 

የተለዩ አካላዊ ገፅታዎች (ባህሪያት) የሚታዩ ሲሆን፣ የአልሞንድ ቅርጽ ያላቸው አይኖች፣ መዳፍ ላይ ያለ መስመር (አሻራ) አንድ አግዳሚ መስመር ብቻ መሆን፣ የፊትና የአፍንጫ አቀማመጥ ከተለመደው ገፅታ ለየት ያለ መሆንን እና የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ።  ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ግለሰቦች የእድገት መዘግየቶች እና እንደ የልብ ጉድለቶች ያሉ አንዳንድ የጤና ችግሮችም ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ። 

ተፅዕኖ፡ 

ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ልጆች አካባቢያዊ ሁኔታዎችን የመረዳት ክህሎት (የሞተር ክህሎቶች) ችግር እና የግንዛቤ እድገትን ጨምሮ ሌሎች ሰፊ የሆኑ የእድገት መዘግየት ሊያመሩ ይችላሊ። 

አካላዊ ባህሪያት፡ 

ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ግለሰቦች ብዙውን ጊዜ ልዩ የሆኑ አካላዊ ባህሪያት አሏቸው። 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *